የጨረታ ማስታወቂያ
ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር Lighting Tower Machine በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ይህንን ማቅረብ የሚችሉ፡-
1 |
ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ |
2 |
ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት የማይመለስ ብር100 /አንድ መቶ/ በመክፈል እስከ 11፡30 ሰዓት ጥር 12,2007ዓ.ም ድረስ በድርጅቱ ግዥ ክፍል 2ተኛፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ |
3 |
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 / ሰላሳ ሽህ ብር/ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታው ፓስታ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡ |
4 |
ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 13, 2007 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ |
5 |
ተጫራቾች ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፓዛል ለየብቻው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ |
6 |
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ |
አድራሻ፡- |
|
ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ከድሪምላይነር ሆቴል ፊት ለፊት፡፡ ስልክ ቁጥር 011-4-66 83 19 011-4-66 83 56 |