የጨረታ ማስታወቂያ

ሱር ኮንስትራክሽን ኃላ.የተ.የግ.ማህበር Lighting Tower Machine በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህንን ማቅረብ የሚችሉ፡-

1. ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

   2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል እስከ 11፡30   ሰዓት ጥር 12,2007ዓ.ም ድረስ በድርጅቱ ግዥ ክፍል 2ተኛፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

   3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 / ሰላሳ ሽህ ብር/ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከጨረታው ፓስታ ጋር ማስገባት አለባቸው፡፡

   4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 13, 2007 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታ፡፡

   5. ተጫራቾች ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ፕሮፓዛል ለየብቻው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡

   6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

            አድራሻ፡- ከደምበል ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ ከድሪምላይነር ሆቴል ፊት ለፊት፡፡

            ስልክ ቁጥር 011-4-66 83 19

                       011-4-66 83 56